ታዋቂ ልጥፎች

ገፆች

ማክሰኞ 19 ኦገስት 2014

(የልጅነት ወግ) ቡሄ ሲመጣ እኔን ትዝ የሚለኝ



አይ ልጅነት! አይ ሆያ ሆዬ! አይ ያሚ ሜዳ … አይ ሞደርን ሰፈር፡፡ አይ ጥይት ቤት .. አይ አይ አይ … ሙልሙል በችርቻሮ የሸጥንበት ጊዜ … 
 
የምንጨፍርበት ዱላችን ከምት ብዛት ሥሩ ሥር ያበቀለ እስኪመስል ጭራሮ ኾኖ፡፡ ዱላ እጁ ላይ ያለቀበት ጨፋሪ እኮ ነበረ መሃላችን፤ … የገነት አቡሽ፡፡ ጠዋት መጨፈር የጀመርን ሰዓት በጨመረ ቁጥር ዱላው እያጠረ፣ እሱም እያጎነበሰ … ማታ ላይ አቡሽ ለምንጨፍርበት ቤት ቤተኞች የአክብሮት ሰላምታ እየሰጠ እንጂ እየጨፈረ በፍጹም አይመስላቸውም ነበር፡፡ እሱም ግን መሬቱን በጣም

ዓርብ 1 ኦገስት 2014

“ሰው ለሰው” ድራማን ሰው ለሰው ያስባለው ምን ይመስላችኋል፤



እንደምን አላችሁ፡፡ እነሆ! ተፈጸመም አይደል፡፡ እኛ ለዘመናት መጨረሻውን ማወቅ ስንናፍቅ መጨረሻውን በሁለት ጣታቸው ይዘው እያሾሩ “እንቁልልጮ!” ሲሉን ... እንደ ጸደይ ጎሕ ቀን በአሳባችን ሌት በሕልማችን እስኪመጣብን ድረስ የናፈቀንን መጨረሻውን አሁን አየንም አይደል፤… ታዲያ አቶ አስናቀ አሸብርም ተንጠለጠሉ አይደል፤የተፋቀረውም ተፋቅሮ

ሐሙስ 24 ጁላይ 2014

ሚስ! ... እባክሽን!





ለእርሷው ለእትዬ የተጻፈ የብሶት ደብዳቤ፡
ይድረስ ኹል ጊዜ ለማስብሽ፣ልጄንም ባየሁ ቊጥር ለምትታወሺኝ ለሚስ


ለጤናሽ እንደምን አለሽ፤ደኅና እንደኾንሽ እገምታለሁ፡፡

እኔ ይኸውልሽ የወላጅና መምህር የተግባቦት መጽሐፍ ላይ የተተወችልኝ ባለ አንድ መስመር አስተያየት መጻፊያ ቦታ ከፊርማ መፈረሚያ አልፋ የሠሙኑን ብሶቴን ለማውጣት አላስፈነጭህ ብትለኝ ጊዜ ደብዳቤ ጻፍኹ፡፡ አማርኛ ማንበብ እንደሚሰለችሽ እረዳዋለሁ፤ነገር ግን

የወራሽ ያለህ!!!



እናንተዬ! እንዴት ጭንቅ ብሎኛል መሰላችሁ፡፡ እንደሁ የ፳ኤል ቅዱስ መላ ይጠቁመኝ እንጂ ምን እላለሁ፡፡ እምላችሁ! እንዲህ እንደኔ ጭንቅ ሲላችሁ ምንድን ነው የምታደርጉት፤ አንዳንዶች ያንጎራጉራሉ፣ይቀኛሉ፣ሌሎች ስንኝ ይቋጥራሉ፡፡ እስቲ ቆይ ስንኝ ልቋጥር፡፡ … እንደውም ለምን እቋጥራለሁ፤በቀደም ለት በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የገጠመኝን አንድ ግጥም ልበልላችሁና ብሶቴን ልወጣ፡፡ አብዲ ሰኢድ ነው አዋሳ ኾኖ በኹለት ሺህ ዓ.ም. ለአቢቲ የላከለት፡፡

ረቡዕ 23 ጁላይ 2014

አማርኛን መተየብ በቀላሉ ይለማመዱ


አማርኛን በቀላሉ መተየብ ይማሩ፡፡ ይህን ሥዕል ለሌሎች ያጋሩት፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ ኹል ጊዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ የአማርኛ የፊደል ሥርዓት ነው፡፡ ባጠቃላይ ሰማንያውም የኢትዮጵያ ብሔረሰብና እሴቶቻቸው መተኪያ የሌላቸው ውዶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን በተቻለን አቅም የእኛው በኾኑ አገር በቀል ነገሮች የመጠቀም ልማዳችንን እናዳብር፡፡ የሌላ ሰው የኾነ

Comment on this