ታዋቂ ልጥፎች

ገፆች

2014 ጁላይ 23, ረቡዕ

አማርኛን መተየብ በቀላሉ ይለማመዱ

አማርኛን በቀላሉ መተየብ ይማሩ፡፡ ይህን ሥዕል ለሌሎች ያጋሩት፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ ኹል ጊዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ የአማርኛ የፊደል ሥርዓት ነው፡፡ ባጠቃላይ ሰማንያውም የኢትዮጵያ ብሔረሰብና እሴቶቻቸው መተኪያ የሌላቸው ውዶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን በተቻለን አቅም የእኛው በኾኑ አገር በቀል ነገሮች የመጠቀም ልማዳችንን እናዳብር፡፡ የሌላ ሰው የኾነ
ነገር የሌላ ነው፤መገልገያችን እንጂ ማንነታችን ሊኾን አይችልም፡፡ የእኛ የኾነ ደግሞ የእኛው ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል በእንግሊዝኛ ቋንቋ እኛ እንገለገልበታለን፡፡ የሚኮሩበት ደግሞ ባለቤቶች አሉት፡፡ እንግሊዛውያን ይባላሉ፡፡ ለእነርሱ ማንነታቸውንም ይገልጽላቸዋል፤ብሔራዊ ኩራታቸውንም ያንጸባርቁበታል፡፡ እኛም ደግሞ የምንገለገልበትም የምንኮራበትም ሰማንያ ቋንቋና ባሕል አለን፡፡ ለዚያውም ደግሞ እንግሊዘኛ ሳይወጠን ጀምሮ በብራና ጭምር የተከተቡ፡፡ ባለቤቶቻቸው ታዲያ ኢትዮጵያውያን የምንባል እኛው ነን፡፡ ምስጋና ለቀደምት አባቶቻችን፤እጆቻቸው ድንቅ ለኾኑ፡፡

[በዚህ አጋጣሚ የኮምፒዩተርና የሌሎች ቴክኖሎጂ ባለሞያዎቻችን በእኛ በኾኑ ነገሮች የመጠቀም ዕድል የሚሰጡንን የሶፍትዌርና የሃርድዌር ቅንብሮችን በመፈልሰፍ የቁርጥ ቀን መኾናችሁን አሳዩ ስል … እስቲ ወንድ የኾነ የታለ! በማለት ጭምር ነው፡፡ .. ሎል] …

የእኔ አቅም ታዲያ ትንሽዬ ናት፤በፌስቡክ ላይ ከመደስኮር አታልፍም፡፡ በቅርቡ ከተወሰነ ሐተታ ጭምር ጋር በማስታወሻ መልክ እመለሳለሁ፤ነገር ግን ለጊዜው ብዙዎች ይህንን ጠቃሚ ኾኖ ያገኙታል ብዬ ስላሰብኩ አጋርቻለሁ፤እንካችሁ! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ ኹል ጊዜ ከሚገርሙኝ ነገሮች አንዱ የአማርኛ የፊደል ሥርዓት ነው፡፡ ባጠቃላይ ሰማንያውም የኢትዮጵያ ብሔረሰብና እሴቶቻቸው መተኪያ የሌላቸው ውዶች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን በተቻለን አቅም የእኛው በኾኑ አገር በቀል ነገሮች የመጠቀም ልማዳችንን እናዳብር፡፡ የሌላ ሰው የኾነ ነገር የሌላ ነው፤መገልገያችን እንጂ ማንነታችን ሊኾን አይችልም፡፡ የእኛ የኾነ ደግሞ የእኛው ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል በእንግሊዝኛ ቋንቋ እኛ እንገለገልበታለን፡፡ የሚኮሩበት ደግሞ ባለቤቶች አሉት፡፡ እንግሊዛውያን ይባላሉ፡፡ ለእነርሱ ማንነታቸውንም ይገልጽላቸዋል፤ብሔራዊ ኩራታቸውንም ያንጸባርቁበታል፡፡ እኛም ደግሞ የምንገለገልበትም የምንኮራበትም ሰማንያ ቋንቋና ባሕል አለን፡፡ ለዚያውም ደግሞ እንግሊዘኛ ሳይወጠን ጀምሮ በብራና ጭምር የተከተቡ፡፡ ባለቤቶቻቸው ታዲያ ኢትዮጵያውያን የምንባል እኛው ነን፡፡ ምስጋና ለቀደምት አባቶቻችን፤እጆቻቸው ድንቅ ለኾኑ፡፡

[በዚህ አጋጣሚ የኮምፒዩተርና የሌሎች ቴክኖሎጂ ባለሞያዎቻችን በእኛ በኾኑ ነገሮች የመጠቀም ዕድል የሚሰጡንን የሶፍትዌርና የሃርድዌር ቅንብሮችን በመፈልሰፍ የቁርጥ ቀን መኾናችሁን አሳዩ ስል … እስቲ ወንድ የኾነ የታለ! በማለት ጭምር ነው፡፡ .. ሎል] …

የእኔ አቅም ታዲያ ትንሽዬ ናት፤እዚህ ላይ ከመደስኮር አታልፍም፡፡ በቅርቡ ከተወሰነ ሐተታ ጭምር ጋር በማስታወሻ መልክ እመለሳለሁ፤ነገር ግን ለጊዜው ብዙዎች ይህንን ጠቃሚ ኾኖ ያገኙታል ብዬ ስላሰብኩ አጋርቻለሁ፤እንካችሁ! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Comment on this